የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የ114 ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥለት ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ በተለያየ የሽብር ወንጀል ተከሰው የሚገኙ የ114 ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥለት ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አቀረበ።

ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዛሬ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት፥ በተለያየ የሽብር ወንጀል ተከሰው የነበሩ 114 ተከሳሾች ክስ ይነሳልኝ ሲል በጽሁፍ አቅርቧል።

የሶደሬኦንድማንድን አፕልኬሽን በማውረድ ፊልሞች ከመለቀቃቸው በፊት ተመልከቱ Download SodereOnDemand app watch full movies before they are released. Apple, Android and Roku SodereOnDemand apps. 

          

ጠቅላይ አቃቢ ህግ የተከሳሾቹ ክስ ከዛሬ ጀምሮ ተቋርጦ ከእስር እንደሚወጡም አስታውቋል።

ሂደቱ መንግስት ከዚህ በፊት ያደረገውን የይቅርታ አሰጣጥ እና ክስ ማቋረጥ ሂደትን የተከተለ ነው ተብሏል።

ክሳቸው እንዲቋረጥ ከተጠየቁ ተከሳሾች መካከልም የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ይገኙበታል።

በታሪክ አዱኛ

About The Author

Related Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published.