ብሔር ብሔረሰቦች በሚለው መዝሙር የሚታወቀው ቢኒያም ኃይለ ሥላሴ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

ታደሰ ገብረማርያም, Reporter

በብዙዎች ዘንድ ብሔር ብሔረሰቦች በሚለው መዝሙሩ የሚታወቀውና የራስ ቴያትር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረው አርቲስት ቢኒያም ኃይለ ሥላሴ ባደረበት ሕመም ዛሬ ጥር 4 ቀን 2010 ዓ.ም. አርፎ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሥርዓተ ቀብሩ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ፡፡ በ46 ዓመቱ ያረፈው የአርቲስት ቢኒያም ሥርዓተ ቀብሩ ቤተሰቦቹ፣ የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡

አርቲስት ቢኒያም ብሔር ብሔረሰቦች ከሚለው መዝሙሩ በተጨማሪ ተንፍሺ አዲስ አበባ፣ ሰራዊት ነንና ሰንደቃችን የተባሉ መዝሙሮችን አበርክቷል፡፡

የሶደሬኦንድማንድን አፕልኬሽን በማውረድ ፊልሞች ከመለቀቃቸው በፊት ተመልከቱ Download SodereOnDemand app watch full movies before they are released. Apple, Android and Roku SodereOnDemand apps. 

          

ነፍሰ ሔር ቢኒያም የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በሰሜን ሸዋ ላሎ ማማ በተባለ ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ አበባ የጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤትና የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከታትሏል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1987 ዓ.ም. በቴያትር ጥበባት እንደተመረቀ በሕፃናትና ወጣቶች ቴያትር ተቀጥሮ ሲሠራ እንደነበር ገጸ ሕይወቱ ያሳይል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.